Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በደኅንነትና በወታደራዊ ቴክኖሎጂ ያሳየችው እመርታ ለአፍሪካውያን ተምሳሌት ነው- የናይጄሪያ ልዑክ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በናይጄሪያ የመከላከያ መረጃ ዋና ኃላፊ ፓርከር አንዳያዳይ የተመራ ወታደራዊ ልዑክ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትን ጎብኝቷል፡፡

ልዑኩ በተጨማሪም በቅርቡ የተመረቀውን የስካይ ዊን ኤሮናቲክስ ኢንዱስትሪን ተመልክቷል፡፡

በዚሁ ወቅትም የናይጄሪያ የመከላከያ መረጃ ዋና ኃላፊ ፓርከር አንዳያዳይ በጉብኝታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በምግብ፣ በኢንዱስትሪ ውጤቶችና በሌሎችም የተለያዩ ዘርፎች እራሷን ለመቻል የምታደርጋቸውን ጥረቶች በደኅንነትና በመከላከያ ቴክኖሎጂዎችም አጠናክራ መቀጠሏ ለአፍሪካ ተምሳሌት መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

የስካይ ዊን ኤሮናቲክስ ኢንዱስትሪ ፕሮጀክት የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን፤ የአፍሪካውያን ጭምር መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ይህም በዘርፉ ከሌሎች ክፍለ-ዓለማት ጥገኝነት ለመላቀቅ መነሳሳት እንደሚፈጥር መግለጻቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የላከው መረጃ አመላክቷል፡፡

የስካይ ዊን ኤሮናቲክስ ኢንዱስትሪ ፕሮጀከት  ብሔራዊ ደኅንነትንና ጥቅምን በማረጋገጥ ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚያበረክት እንዲሁም ሉዓላዊነትንም ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.