ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ቱሪዝምን ለማሳደግ የሚያግዛትን ስምምነት ፈረመች
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍን ለማሳደግ የሚያስችላትን ስምምነት በአፍሪካ ጉዞና ቱሪዝምን ለማስፋፋት ከሚሠራው አፍሪካ ትራቭል ኮኔክት ጋር ስምምነት ፈርማለች፡፡
ስምምነቱን የፈረመው በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በማኅበራዊ ትሥሥር ገፁ ባወጣው መረጃ፤ ስምምነቱ በርካታ ዕድሎችን የሚፈጥር ነው፡፡
ይህም የሀገሪቱን ልዩ እና ማራኪ መዳረሻዎች በማስተዋወቅ ተደራሽነትን እንደሚጨምር ገልጿል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ቅርሶቿንና መልክዓ-ምድሮቿን እንዲሁም ልዩ የቱሪዝም መዳረሻዎቿን በማስተዋወቅ፤ በአፍሪካ ቀዳሚ የጉዞ መዳረሻ ለመሆን ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ብሏል፡፡