Fana: At a Speed of Life!

የቱርክ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚፈልጉ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱርክ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡

በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሃመድ በተለያዩ ዘርፎች ከተሰማሩ የቱርክ ኩባንያዎች ተወካዮችና ባለሃብቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደሩ በዚሁ ወቅት፥በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን፣ የፋይናንስ ዘርፉንና የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ባለሃብቶቹ ለተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው፥ በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች መሰማራት እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኩባንያዎች በቅርቡ በኢትዮጵያ በሚካሄዱት የኢትዮጵያ ታምርት እና ኢንቨስት ኢትዮጵያ የቢዝነስ ፎረሞች ላይ እንዲሳተፉ አምባሳደሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.