የአማራ ክልል የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል አጀንዳ የማሠባሠብ ሥራውን እያከናወነ ነው።
የወረዳ ማኅበረሰብ ተወካዮች የአጀንዳ ማሠባሠብና ለአጠቃላይ የምክክር ጉባዔው ወኪሎችን የመምረጥ ሥራ ሚያዝያ 1 ቀን 2017 ዓ.ም መጠናቀቁ ይታወሳል።
በዛሬው ዕለት ደግሞ አምስት ባለድርሻ አካላትን ያካተተው ክልላዊ የምክክር መድረክ መጀመሩ ነው የተገለጸው፡፡
በምክክር ሒደቱ የመንግሥት ተቋማት ተወካዮች፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ማኅበራት ተወካዮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና በመጀመሪያው ዙር ምክክር ለሀገራዊ የምክክር ጉባዔ የተመረጡ የወረዳ ማኅበረሰብ ወኪሎች ተሳትፈዋል፡፡