Fana: At a Speed of Life!

የተቀናጀ የጭነት ትራንስፖርት አስተዳደር ሥርዓት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የተቀናጀ የጭነት ትራንስፖርት አስተዳደር ሥርዓትን አስመርቋል፡፡

ሥርዓቱ የትራንስፖርት ኦፕሬተርነት ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥን ከተሽከርካሪና አሽከርካሪ መረጃ ጋር በማቀናጀት ለማስተዳደር ያስችላል ተብሏል።

ከአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር የለማው የተቀናጀ የጭነት ትራንስፖርት አስተዳደር ሥርዓት÷ የተሽከርካሪዎችን፣ አሽከርካሪዎችንና የረዳቶችን የድንበር ተሻጋሪ ፈቃድ አሰጣጥ በተቀናጀ ሁኔታ ለመስጠት የሚያሥችል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመሠረታዊነት ሊፈታ የሚችል ሥርዓት እንደሆነም ተገልጿል።

የትራንስፖርት አስተዳደር ሥርዓቱ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተመርቋል፡፡

 

 

በፌቨን ቢሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.