Fana: At a Speed of Life!

ኅብረቱ ሰላምን ለማስፈን የሚያደርገውን ጥረት የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች እንድትደግፍ ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ በኢትዮጵያ የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች አምባሳደር ሞሀመድ ሳሌም አል ረሺድ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በአፍሪካ ኅብረት እና በተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በአፍሪካ በቁልፍ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ያላትን ተሳትፎ ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም ውይይት አድርገዋል፡፡

መሃሙድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት÷ በአፍሪካ ኅብረት ተነሳሽነት የሚካሄዱ የሰላም እና መረጋጋት ተልዕኮዎችን የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች እንድትደግፍ ጠይቀዋል፡፡

አምባሳደር ሞሀመድ ሳሌም አል ረሺድ በበኩላቸው÷ ሀገራቸው ከአፍሪካ ኅብረት ጋር የምታደርገውን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ማረጋገጣቸውን ከኅብረቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.