Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) የሆሚቾ ኦሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሆሚቾ ኦሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም በመከላከያ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችንና የተለያዩ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

ሚኒስትሯ ከጉብኝቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት ኢንዱስትሪው ኢትዮጵያ በመከላከያ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እያሳየች ላለችው እመርታ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በኢንዱስትሪው እየተመረቱ ያሉ ምርቶች የሰራዊቱን ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር ኢትዮጵያ በወታደራዊ ምርቶች ራሷን እንድትችል ለማድረግ ከተቀመጠው ግብ አኳያ የጎላ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ሀገራዊ ልማትን ለመደገፍ ብሎም ጠንካራና ራሱን የቻለ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ለመገንባት ያለንን አቅምና ቁርጠኝነት ያሳየንበት ነው ብለዋል፡፡

የሆሚቾ ኦሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንና ዘመናዊ የምርት ስርዓት በመዘርጋት ላሳየው እመርታ የኢንዱስትሪ ግሩፑና የኢንዱስትሪው አመራሮችና ሰራተኞችን ትጋት አድንቀዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንዱስትሪውን በመደገፍ ሥራውን ለማጠናከር ቃል መግባታቸውንም ከመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.