አየር መንገዱ የአውሮፕላን መቀመጫዎችን ለመግዛት ስምምነት ተፈራረመ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዜድ-400 የተሰኙ የአውሮፕላን መቀመጫዎችን ለመግዛት ሳፍራን ከተባለ የአውሮፕላን ቁሳቁስ አምራች ኩባንያ ጋር ስምምነት መፈራረሙን ገልጿል፡፡
በስምምነቱ መሰረት ኩባንያው ለአየር መንገዱ ስምንት የቦይንግ 777-9 አውሮፕላኖች ኢኮኖሚ ክፍል የሚሆኑ መቀመጫዎችን እንደሚያቀርብ ታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተመረጡት Z400 መቀመጫዎች ለተሳፋሪዎች የተሻለ ምቾት የሚሰጡ መሆናቸውንም ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡