Fana: At a Speed of Life!

ባህር ዳር ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ24ኛው ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

አመሻሽ 12 ሠዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የባህር ዳር ከተማ ማሸነፊያ ግቦችን ቸርነት ጉግሳ እና ፍፁም አለሙ ማስቆጠር ችለዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ባሕር ዳር ከተማ በ37 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ÷ ኢትዮጵያ ቡና በ36 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

በዛሬው የሊጉ መርሐ ግብር ቀን 9 ሠዓት ላይ አርባ ምንጭ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

በዚሁ ጨዋታ ታምራት እያሱ ለአርባምንጭ ከተማ እንዲሁም ዳዊት ዮሐንስ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንዳንድ ግብ ማስቆጠር ችለዋል፡፡

በሊጉ የደረጃ ሠንጠረዥ ኢትዮጵያ መድን፣ ባሕር ዳር ከተማ እና ወላይታ ድቻ ከአንድ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ÷ አዳማ ከተማ፣ ስሑል ሽረ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ወራጅ ቀጣና ላይ የሚገኙ ክለቦች ናቸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.