Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም የ5G የሞባይል ኔትወርክ በባሌ ሮቤ እና አሰላ ከተሞች አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የአምስተኛው ትውልድ (5ጂ) ኔትወርክ ማስፋፊያ ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል በዛሬው ዕለት በባሌ ሮቤና አሰላ ከተሞች አገልግሎቱን በይፋ አስጀምሯል፡፡

በተጨማሪም በደቡብ ምስራቅና ደቡብ-ደቡብ ምስራቅ ሪጅኖች በሚገኙ 114 ከተሞች የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን መጠቀም የሚያስችለውን ዘመናዊውን የ4ጂ ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ተጀምሯል፡፡

የከተሞቹ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት የአምስተኛ ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ ተጠቃሚ ከተሞችን ወደ 16 አሳድጎታል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዚሁ ወቅት፥ ኩባንያው አገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን የማድረግ ጉዞ ላይ ይገኛል ብለዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት የደቡብ ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ጽሕፈት ቤት አገልግሎትም አስጀምሯል።

በቅድስት አባተ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.