Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የብየዳ ጉባዔን ታስተናግዳለች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከሚያዝያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት ሦስተኛው የአፍሪካ ብየዳ ጉባዔና ዓለም አቀፍ ኮንፈረስ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢኒስቲትዩት የዓለም አቀፍ ቴክኖሎጂ ማምረትና ብየዳ ልኅቀት ማዕከል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰላሙ ይስሃቅ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ፤ በጉባዔው ላይ ከ16 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 43 የብየዳ ክኅሎት ባለሙያዎች የብየዳ ውድድር ይካሄዳል፡፡

በውድድሩ ኢትዮጵያ በ21 ተወዳዳሪዎች እንደምትወከልም አብራርተዋል፡፡

ከአፍሪካ ውጪ ከሚገኙ ሥድስት ሀገራት የሚመጡ የብየዳ ባለሙያዎችና የዘርፉ ዓለም አቀፍ ተቋማት አመራሮች  በጉባዔው እንደሚሳተፉ ጠቁመው፤ ሥድስት ጥናታዊ ጽሑፎች እንደሚቀርቡ ጠቁመዋል፡፡

የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢኒስቲትዩት በትብብር ያዘጋጁት ይህ ጉባዔ፤ “የአፍሪካ የብየዳ ሙያን በማጎልበት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ማረጋገጥ” በሚል መሪ ሐሳብ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

በእዮናዳብ አንዱዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.