Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ሕብረት ከኢትዮጵያ ጋር ላለው ግንኙነት የተለየ ትኩረት እንደሚሰጥ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሕብረት ከኢትዮጵያ ጋር ላለው ግንኙነት የተለየ ትኩረት እንደሚሰጥ የሕብረቱ ውጭ ግንኙነት አገልግሎት የኢኮኖሚ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሐፊ ሳይመን ሞርዱ አረጋገጡ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከሳይመን ሞርዱ ጋር ተወያይተዋል።

በዚሁ ወቅት በኢትዮጵያ እና አውሮፓ ሕብረት መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በየጊዜው ምክክር ማድረጉ ጠቃሚ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ፤ በቀጣናዊ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ገለጻ አድርገዋል።

ኢትዮጵያ እና ሕብረቱ በፈረንጆቹ 2016 የተፈራረሙትን ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋርነት በይበልጥ ማጠናክር እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል፡፡

ሳይመን ሞርዱ በበኩላቸው፤ ሕብረቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአፍሪካ ሕብረት ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር እንደሚፈልግ አረጋግጠዋል፡፡

የአውሮፓ ሕብረት ከኢትዮጵያ ጋር በኢኮኖሚ የልማት ትብብር፣ በሥራ ፈጠራ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች የሚያደርገው ትብብር ከሁለትዮሽ ግንኙነት ባለፈ ቀጣናዊ ፋይዳ እንዳለውም አብራርተዋል።

በመሆኑም የአውሮፓ ሕብረት ከኢትዮጵያ ጋር ላለው ግንኙነት የተለየ ትኩረት ይሰጣል ማለታውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.