ተማሪዎች የሀገሪቱን የነገ ዕጣ ፋንታ የሚያሳምር እውቀት መቅሰም አለባቸው – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጠንክረው በመማር የሀገሪቱን የነገ ዕጣ ፋንታ የሚያሳምር ብሩህ አዕምሮ መያዝ አለባቸው ሲሉ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አሳሰቡ፡፡
ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ በትምህርት ዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም በጂንካ ከተማ የኤሶል ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና የጂንካ 2ኛ ደረጃ ትምህር ቤትን የመማር ማስተማር ሒደት ተመልክተዋል።
በዚህ ወቅትም ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጠንክረው በመማር የሀገርቱን የነገ ዕጣ ፋንታ የሚያሳምር እውቀት መገብየት እንዳለባቸው ማስገንዘባቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።