Fana: At a Speed of Life!

በተመረጡ 222 ወረዳዎች የወባ ሥርጭትን ለመቀነስ በትኩረት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ10 ክልሎች በተመረጡ 222 ወረዳዎች ላይ የወባ ሥርጭትን መቀነስ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ጉዲሳ አሰፋ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷የወባ ሥርጭትን ለመቀነስ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገ ርብርብ ውጤት ተመዝግቧል፡፡

በሀገሪቱ ከፍተኛ የወባ ሥርጭት ያለባቸው 222 ወረዳዎች መለየታቸውን ጠቁመው÷በእነዚህ አካባቢዎችም ሥርጭቱን ለመቀነስና ከምንጩ ለማጥፋት የሚያስችል ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

በሚኒስቴሩ የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር ም/ዋና ዳይሬክተር አክልሉ ጌትነት በበኩላቸው÷ከዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች 50 ሚሊየን ብር ለማህበሩ ድጋፍ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም በክልሎች በዘርፉ ከተሰማሩ ሀገር በቀል ድርጅቶች ጋር በትብብር ለመስራት መግባቢያ ሰነድ ተፈርሞ ወደ ሥራ መገባቱን ነው ያመላከቱት፡፡

በተካልኝ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.