Fana: At a Speed of Life!

114 ተጨማሪ ከተሞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ኔትወርክ ተጠቃሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በባሌ ዞን፣ አርሲ ዞን፣ ምስራቅ ባሌ ዞን፣ ምዕራብ አርሲ ዞን እና ምስራቅ ሸዋ ዞን በሚገኙ 114 ተጨማሪ ከተሞች የላቀ ፍጥነት ያለው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ተጠቃሚ አደረገ፡፡

ተቋሙ ሲያከናውን የነበረውን መጠነ ሰፊ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ኔትወርክ ማስፋፊያ ፕሮጀክት በማጠናቀቅ በደቡብ ምስራቅ ሪጂን 58 እንዲሁም በደቡብ ደቡብ ምስራቅ ሪጂን 56 በድምሩ 114 ከተሞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ኔትወርክ የላቀ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት ግንኙነትን እውን በማድረግ፤ አዳዲስ ዕድሎችን በመክፈት ለአካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተብራርቷል።

ኢትዮ ቴሌኮም የላቀ የኢንተርኔት ፍጥነት በመላ ኢትዮጵያ በማስፋፋት አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ በመገንባት ረገድ የበኩሉን ሚና መጫወቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ አመላክቷል፡፡

https://bit.ly/4lmShKp

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.