Fana: At a Speed of Life!

ውጤታማ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሁለተኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማካሄድ የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ህብረት የግብርና እና ገጠር ልማት ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ ጋር ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን ሁለተኛውን የአፍሪካ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን በተመለከተ ተወያይተዋል።

በውይይቱ ጉባኤው የአፍሪካ የአየር ንብረት አጀንዳ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጣ ለማስቻል እንደሚሰራ ተገልጿል።

ሁለቱ ወገኖች ጉባኤው ትርጉም ያለው እንዲሆን ለመድረግ በቅንጅት እና በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

ጉባኤው በአህጉሪቱ ዘላቂ እድገት እንዲመጣ ብሎም የአየር ንብረት ለውጥ ጫናን ለመቀነስ የሚያስችል ሥራ ለመስራት ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል።

እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ጫና ለመቋቋም በህብረት የአህጉሪቱን ድምጽ ለማሰማት ጉባኤው የጎላ ሚና እንዳለው ነው የተጠቆመው፡፡

ሁለተኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በመጪው መስከረም በአዲስ አበባ የሚካሄድ መሆኑን የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.