Fana: At a Speed of Life!

ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ከጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስትር ረዳት ጸሃፊ ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ከጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስትር ረዳት ጸሃፊ ኔይልስ አነንጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ጀርመን በአፍሪካ በጤና፣ ሰላምና ጸጥታ ዘርፍ እንዲሁም በቀጣናዊ ውህደት ጥረቶች ዙሪያ  የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ በምትቀጥልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

ማህሙድ አሊ ዩሱፍ÷ጀርመን በአፍሪካ ህብረት በኩል ለምታደርገው የባለብዙ ወገን ትብብርና ከአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ጋር ያላትን ጠንካራ ግንኙነት አድንቀዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች ዓለም አቀፍ ብዝሃነትን ለማረጋገጥ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ አጽንኦጽ ሰጥተዋል፡፡

ዘላቂ ልማትን፣ የንግድ ትስስርን እና የጋራ እድገትን ለማምጣት ተቋማቱ በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ መግለጻቸውንም የህብረቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.