Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና አርሜኒያ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የአርሜኒያ አምባሳደር ሳሃክ ሳርግስያን የተመራ ቡድን በኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሥራ ጉብኝት አድርጓል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቼና (ዶ/ር) እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ቡድኑን ተቀብለው የተቋሙን የሥራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

አምባሳደር ሳሃክ ኢትዮጵያ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፉን ለማሳደግ በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኗን አድንቀዋል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ላሉ ሀገራት የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና የዲጂታላይዜሽን ትብብርን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ጥሩ አጋር መሆኗን ገልፀዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ ከጉብኝቱ በኋላ ከኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር የትብብር መስኮችን በማስፋት ላይ ያተኮሩ ጥልቅ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፤ ሀገራቱ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸውን የኢንስቲትዩቱ መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.