Fana: At a Speed of Life!

በማህበራዊ ሚዲያዎች ሊደርሱ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን እንዴት መከላከል ይቻላል?

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማህበራዊ ሚዲያዎችና በኢንተርኔት የሚፈጸሙ የማጭበርበር እንቅስቃሴዎች እየበረከቱ ይገኛሉ።

መሰል የዲጂታል ማጭበርበሮችን ለመከላከል ልንወስዳቸው የሚገቡ የጥንቃቄ ርምጃዎች ያሉ ሲሆን÷ ከእነዚህ መካከልም የሚከተሉት ይገኙበታል፦

👉 ያልታወቁ አድራሻዎችን ወይም ሊንኮችን ከመክፈት በመቆጠብ፤

ከላይ ያሉትን ወይም ተመሳሳይ አድራሻዎች በመልዕክት፣ በማህበራዊ መገናኛ፣ ወይም በሌላ መንገድ ከደረስዎ ከመክፈት መቆጠብ በተለይ “እንኳን ደስ ያለህ! ገንዘብ አሸንፈሃል፣ ይህን አገናኝ ጫን” የሚል መልዕክት ከመጣ፣ ይህ ማጭበርበሪያ ሊሆን ስለሚችል መጠንቀቅ፣

👉የሞባይል እና የባንክ መረጃዎችን ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በመጠቀም፤ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎችን ከታመኑ ምንጮች (እንደ Google Play) ወይም አፕስቶር (app-store) ብቻ ያውርዱ፣

👉 የይለፍ-ቃልዎን ወይም የባንክ መለያዎችን ባልታወቁ ድረ-ገፆች ከማስገባት መቆጠብ፤

👉 በዲጂታል ሚዲያዎች አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከቱ ሪፖርት በማድረግ፣ እንደዚህ አይነት መልዕክቶች ወይም አድራሻዎች ካዩ ወዲያውኑ ለEthio-CERT በኢ-ሜይል (ethiocert@insa.gov.et) ወይም በስልክ (933) ያሳውቁ፣

👉በነፃ Wi-Fi ስንጠቀም በጥንቃቄ በመጠቀም፤ በካፌዎች፣ በሆቴሎች፣ ወይም በሌሎች የህዝብ ቦታዎች ያለውን ነፃ Wi-Fi ሲጠቀሙ፣ የግል መረጃዎችን አያስገቡ፣

#የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.