አምራች ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፍ ማድረግ ይገባል – ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አምራች ኢንዱስትሪዎች የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ይገባል ሲሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለፁ።
የ2017 ዓ.ም የአምራች ኢንዱስትሪዎች አውደ ርዕይ “ከሸማችነት ወደ አምራችነት” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ነው፡፡
ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በማቃለል የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ሊደገፉ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ማነቆ የሆኑ የማምረቻ ቦታ ችግሮችን ለመፍታት የክላስተር አሰራር ሊተገበር ይገባል ነው ያሉት፡፡
አምራች ኢንዱሰትሪዎች ከፋይናንስ አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚያጋጠሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ባንኮች አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም አምራች ኢንዱስሪዎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የተቀናጀ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡
ከአውደ ርዕዩ ጎን ለጎን በዘርፉ ያሉ መልካም ተሞክሮዎች እና ተግዳሮቶች ላይ የሚያተኩር የባለድርሻ አካላት ፎረም በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ የኮርፖሬኑ መረጃ ያመላክታል፡፡