የኢትዮጵያውያን አትሌቶች የአለም ሻምፒዮና ማጣሪያ በስፔን ይደረጋል-ኮማንደር ስለሺ ስህን
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ10 ሺህ ሜትር ኢትዮጵያን በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለመወከል በስፔን ማላጋ የማጣሪያ ውድድር እንደሚደረግ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አስታውቋል፡፡
የፌዴሬሽኑፕሬዚዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ ከ10 ሺህ ሜትር ውጪ ባሉ ርቀቶች አትሌቶች በሀገር ውስጥ በሚደረገው የኢትዮጵያ ሻምፒዮና ይመረጣሉ፡፡
ለዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ10 ሺህ ሜትር ማጣሪያ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ በስፔን ማላጋ መደረጉ የሚታወስ ነው።
የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በፈረንጆቹ ከቀጣዩ መስከረም 3 እስከ 11 ቀን በጃፓን ቶኪዮ ይካሄዳል፡፡
በሰለሞን በቀለ