Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል የምክክር አጀንዳ ርክክብ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል የምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ ማጠቃለያ እና የምክክር አጀንዳ ርክክብ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡

በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች እና በአጀንዳ ማሰባሰቡ ሒደት የተሳተፉ ተወካዮች ተገኝተዋል።

በአማራ ክልል ከመጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ በሁለት ምዕራፎች ሲካሄድ ቆይቷል።

በምክክሩ የመጀመሪያ ምዕራፍ 10 የሕብረተሰብ ክፍሎችን የወከሉ ከ4 ሺህ 500 በላይ ተወካዮች አጀንዳዎችን የመሰብሰብ እና የመለየት ሥራ አከናውነዋል።

በሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግሥት አካላት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ ተቋማት አና የማኅበራት ተወካዮች ሲሳተፉ ቆይተዋል።

ከአማራ ክልል የምክክር ባለድርሻ አካላት የተመረጡ 25 ወኪሎች የተጠናቀረውን የአማራ ክልል አጀንዳ ለዋናው መድረክ አቅርበዋል፡፡

በተወካዮቹ የቀረበው አጀንዳ ከተሳታፊዎች በሚነሱ ሀሳቦች ዳብሮ ለኮሚሽኑ እንደሚረከብ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.