Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 9 ወራት በመትጋታችንና በመልፋታችን የሚታይና የሚጨበጥ ውጤት አስመዝግበናል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተመዘገቡ ስኬቶች ሳንዘናጋ ለላቀ ውጤት መትጋት አለብን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የካቢኔ አባላት በተገኙበት የመንግሥት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፥ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከዕቅድ በላይ አፈጻጸም መመዝገቡን ገልጸዋል።

በመትጋታችንና በመልፋታችን የሚታይና የሚጨበጥ ውጤት አይተናል ነው ያሉት።

በእያንዳንዱ ዘርፍ የተገኘው ውጤት ለተጨማሪ ጥረት የሚያነሳሳ እና ሀገራዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

የካቢኔ አባላት ስኬት ሳያዘናጋቸው ተጨማሪ ትጋት ፈጥረው ሊሰሩ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በለውጥ ሒደት ስኬት ጉዞን የሚገታ ወጥመድ መሆኑን ጠቅሰው፥ አሁን የተሳኩ ውጤቶች እንዳያዘናጉን መጠንቀቅ ይገባል ነው ያሉት።

ተሳክቶልኛል የሚል እሳቤ ከተፈጠረ የሚደረጉ ተጨማሪ ትጋቶችን በመቀነስ ለውጡ የሚጠበቀውን ውጤት እንዳያመጣ ያደርጋል ብለዋል።

በመሆኑም የተገኘውን ስኬት ለተጨማሪ ትጋት መጠቀምና በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ከታቀደው በላይ ለማሳካት መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.