ማንቼስተር ሲቲ ከመመራት ተነስቶ ክሪስታል ፓላስን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ 32ኛ ሳምንት ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ከመመራት ተነስቶ ክሪስታል ፓላስን 5 ለ 2 አሸንፏል፡፡
በምሳ ሰዓት በተደረገው ጨዋታ ክሬስታል ፓላስ በኤዜ እና ሪቻርድስ ግቦች 2 ለ 0 መምራት ቢችልም ኬቨን ዴብሮይን እና ኦማር ማርሙሽ አከታትለው ባስቆጠሯቸው ግቦች በ2 አቻ ውጤት ወደ እረፍት አምርተዋል፡፡
ከእረፍት መልስ የጨዋታ ብልጫ የነበራቸው ሲትዝኖቹ ኮቫቺች፣ ጆን ማክ አቲ እና ኦሬሊባስቆጠሯቸው ግቦች 5 ለ 2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል፡፡