Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ዕዳ ከጂዲፒ ጋር ያለው ምጣኔ ወደ 13 ነጥብ 7 ከመቶ መድረሱ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ የውጭ ምንዛሬ አሰራር መዘርጋቱም ከውጭ የሚላክ የውጭ ምንዛሪ እንዲጨምር በማድረግ የሀገራችንን የውጪ ምንዛሬ ክምችት እንዲጨምር ማስቻሉ ተገልጿል።

በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የ2017 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የአፈፃፀም ግምገማ መካሄድ ጀምሯል።

በመርሐ ግብሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም አቅርቦትን በመመልከት የጀመረ ሲሆን÷ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያ በሀገር ውስጥ አኢኮኖሚ ላይ ያለው ተፅዕኖ አጠቃላይ ምልከታ ቀርቦበታል።

በመካሄድ ላይ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ርምጃ ወቅታዊ መረጃ የቀረበ ሲሆን÷ የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም መርሐ ግብር የተረጋጋ ሆኖ የቁጠባ እና የኢንቨስትመንት እድገት ማሳየቱ ተጠቅሷል።

እንዲሁም የውጭ ዕዳ ከሀገራዊ የምርት መጠን (ጂዲፒ) ያለው ምጣኔ ወደ 13 ነጥብ 7 ከመቶ በመድረስ ትርጉም ባለው መጠን መቀነሱ ተገልጿል።

አዲስ የውጭ ምንዛሬ አሰራር መዘርጋቱ ከውጭ የሚላክ የውጭ ምንዛሪ እና ክምችት እንዲጨምር ማስቻሉ ነው የተጠቆመው፡፡

ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም ከግብርና፣ ከማዕድን፣ ከኢንደስትሪ እና ኤሌክትሪክ የተገኙ የውጭ ንግድ ገቢዎችም እድገት ማሳየታቸው ተገልጿል።

ቡና፣ ወርቅ፣ ጥራጥሬ፣ የዘይት ምንጭ ፍሬዎች፣ አበባ እና ኤሌክትሪክ አምስቱ ቀዳሚ የውጭ ንግድ ምርቶች መሆናቸውም ተመላክቷል።

በተጨማሪም የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ፕሮጀክት 98 ነጥብ 66 ከመቶ አፈፃፀም ላይ መድረሱ እና ስድስት ዩኒቶቹም ወደ ስራ መግባታቸው ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.