Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ ለአርሶ አደሩ እንዲደርስ ዩኒየኖች በትኩረት እንዲሰሩ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ ለአርሶ አደሮች እንዲደርስ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየኖች በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ሲል የግብርና ሚኒስቴር አሳሰስቧል፡፡

የግብርና ሚኒስትር ዴዔታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር÷በቢሾፍቱ አካባቢ ለውጭ ገበያ የሚቀርብ በ78 ሄክታር መሬት ላይ እየለማ የሚገኝ ሹገር ስናብ እና ማንጄቱት የተሰኙ የአትክልት ማሳዎችን ጎብኝተዋል።

በተጨማሪም በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ በማዕከላዊ መጋዘንና በመሰረታዊ የገበሬዎች የህብረት ሥራ ዩኒየኖች በኩል የሚደረገውን የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ሥርጭት ሒደት ተዘዋወረው ተመልክተዋል፡፡

ሚኒስትር ዴዔታዋ በዚህ ወቅት÷ በአፈር ማዳበሪያ ሥርጭት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመከታተል መፍታት እደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ ለተጠቃሚው አርሶ አደር ተደራሽ እንዲሆን የህብረት ሥራ ዩኒየኖች በትኩረት እንዲሰሩ ማሳሰባቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.