Fana: At a Speed of Life!

በሶማሊያ የተሰማራው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ውጤታማ ሥራ እያከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሊያ የተሰማራው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ውጤታማ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል ኃላፊ ሜ/ጀ አዳምነህ መንግስቴ በሶማሊያ የተሰማራውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እንቅስቃሴ በባይደዋ ሴክተር 3 በመገኘት ተመልክተዋል፡፡

ሜጀር ጀኔራሉ በዚሁ ወቅት በሁሉም መስክ ተልዕኳቸውን እየተወጡ የሚገኙ የሴክተር 3 አመራርና አባላት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በመስራት ለትልቅ ድል መብቃትን በተግባር በማሳየታቸው አመስግነዋል፡፡

የሶማሊያ የፀጥታ ሃይል ሀገራቸውንና ሕዝባቸውን ከአልሸባብ እንዲከላከሉ በማብቃትና ተልዕኮን በጋራ በመወጣት ውጤታማ ሥራ እንደተሰራ ማንሳታቸውንም የመከላከያ ሰራዊት መረጃ አመላክቷል።

አልሸባብ እኩይ ተግባሩን ማሳካት እንዳይችል ከማድረግ ባለፈ የሕዝቡን ባህልና ወግ አክብራችሁ ተልዕኳችሁን መወጣት በመቻላችሁ ሀገራችሁና ተቋማችሁ ኮርተውባችኋል ሲሉም አድንቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.