Fana: At a Speed of Life!

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ 4 ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ32ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ 4 ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ይበልጥ እየቀረበ ያለው ሊቨርፑል ቀን 10 ሰዓት ዌስትሃምን በአንፊልድ የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል።

ሊቨርፑል የዛሬውን ጨዋታ ጨምሮ ከቀሩት ሰባት ጨዋታዎች 9 ነጥብ ማግኘት ከቻለ የሌሎች ክለቦችን ውጤት ሳይጠብቅ ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋግጣል።

በተመሳሳይ 10 ሰዓት ቼልሲ የቀጣይ ዓመት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎን እያለመ በወራጅ ቀጣና የሚገኘውን ኢፕስዊች ታውንን በስታንፎርድ ብሪጅ ያስተናግዳል።

ዎልቭስ ከቶተንሃም ሆትስፐር በተመሳሳይ 10 ሰዓት የሚገናኙ ሲሆን፥ ምሽት 12፡30 ማንቼስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጭ ኒውካስል ዩናይትድን ይገጥማል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.