3 ሺህ 367 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 367 ኢትዮጵያውያን በዚህ ሳምንት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በሳምንቱ በተደረጉ ዘጠኝ በረራዎች የተመለሱት ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆን÷ ከተመላሾች መካከል 18 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።
በ4ኛው ዙር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 50 ሺህ ዜጎችን ለመመለስ ታቅዶ መጋቢት 3/2017 ዓ.ም በተጀመረው መርሐ ግብር 15 ሺህ 684 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር መመለሳቸው ተገልጿል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ የማድረግና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ መሆኑንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡