Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለት ሽልማቶችን ተቀዳጀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ “በአፍሪካ ምርጥ የበረራ ላይ ምግብ አቅርቦት አየር መንገድ” ሽልማት እና በአፍሪካ በቀዳሚነት በተረከባቸው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላኖቹ በሚሰጣቸው ዘመናዊ አገልግሎቶች ሽልማትን ተቀዳጅቷል፡፡

እነዚህ ሽልማቶች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ እውቅና ያጎናፀፉና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ተወዳዳሪነት እንደሚያጠናክሩ ተገልጿል፡፡

የሁለቱ ሽልማቶች መርሐ ግብሮች በጀርመን ሀምቡርግ ከተማ መካሄዳቸውን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.