Fana: At a Speed of Life!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በ26ኛ መደበኛ ስብሰባው የ2017 በጀት ዓመት የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ላይ እየመከረ ነው።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በስብሰባው በክልሉ መንግስት የታቀዱ ስራዎች በተቀመጠላቸው አላማ እና ግብ መሰረት ተፈጻሚ ስለመሆናቸው በዝርዝር ይመከርባቸዋል ብለዋል።

በክልሉ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶች፣ የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል የተከናወኑ ተግባራት፣ ከተሞችን ለማዘመን የተጀመሩ ስራዎች፤ በስራ እድል ፈጠራ ላይ ስለተከናወኑ ስራዎች ውይይት እንደሚካሄድም አብራርተዋል።

የዜጎች በሽታ መከላከል እና ህክምና፣ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የተከናወኑ ተግባራት፣ የገቢ አቅምን ማጎልበት እና ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ ከመሰብሰብ አንጻር እንዲሁም የሰላምና ጸጥታ ስራዎች እንደሚነሱም አመላክተዋል።

እንዲሁም የመሰረተ ልማት አውታሮች ያሉበት ደረጃ፣ በኢንቬስትመንት ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትና ያስገኙት ውጤት አፈጻጸም በዝርዝር እንደሚታይ እና ከኢኮኖሚ ግንባታ፣ ከዘላቂ ሰላም ግንባታ፣ ከማህበራዊ የህዝብ ተጠቃሚነት፣ የመሰረተ ልማት ስራዎች ያስገኙት ውጤት ላይ ዝርዝር ግምገማ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

በአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ስለመቻሉ ምክክር እንደሚደረግ እና የሴክተር መስሪያ ቤቶች፣ የዞኖችና የልዩ ወረዳዎች አፈጻጸም ደረጃ እንደሚለይ ገልጸዋል።

መስተዳድር ምክር ቤቱ በሁለተኛ አጀንዳው በክልሉ ለውሳኔ የቀረቡ የኢንቬስትመንት ፍላጎቶች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.