Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ብራዚል የሰላም እና ደህንነት ትብብራቸውን ለማጠናከር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ብራዚል ያላቸውን ታሪካዊ ግንኙነት በሰላም እና ደህንነት ዙሪያ ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት ተካሂዷል።

በብራዚል የኢትዮጵያ አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ከብራዚል የመከላከያ ሚኒስትር ጆዜ ሙሲዮ ሞንቴሮ ፊልሆ ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ልዑልሰገድ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ ከሚኒስትሩ ጋር የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት በሰላም እና ደህንነት ዘርፍ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን አስታውቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.