Fana: At a Speed of Life!

3ኛው የአፍሪካ ብየዳ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሶስተኛው የአፍሪካ ብየዳ ፌዴሬሽን ዓመታዊ ጉባዔና ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በጉባዔው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፣ የአፍሪካ ብየዳ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት መሐመድ አብደል-አሊም (ፕ/ር) እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

16 የአፍሪካ ሀገራት የሚሳተፉበት ጉባዔው “አፍሪካን ማብቃት ለክልላዊ ውህደት እና ለዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የብየዳ አቅምን ማጠናከር” በሚል መሪ ሃሳብ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል።

ጉባዔውን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የቴክኒክ ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት እንዲሁም የአፍሪካ ብየዳ ፌዴሬሽን በጋራ አዘጋጅተውታል።

በጉባዔው የብየዳ ሙያን በተመለከተ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ተገልጿል።

በተጨማሪ ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሚቀርቡበት እንዲሁም የልምድ ልውውጥ የሚደረግበት እና ትስስር የሚፈጠርበት መድረክ እንደሚሆን ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.