Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ለትንሳዔ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር በቅንጅት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በትንሳዔ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ የኑሮ ውድነትና ሕገ-ወጥነት መከላከል ግብረ ኃይል ለመጪው የትንሳኤ በዓል ከምርት አቅርቦት ጋር ተያይዞ የተከናወኑ ሥራዎችን ገምግሟል፡፡

አቶ ጃንጥራር አባይ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ለትንሳዔ በዓል የተረጋጋና ፍትሃዊ የሆነ የግብይት ሥርዓት እንዲኖር አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

ለበዓሉ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች፣ የኢንዱስትሪ ምርት ውጤቶች፣ የግብርና ውጤቶች እና የቁም እንስሳት አቅርቦት በበቂ ሁኔታ መዘጋጀቱን አስረድተዋል፡፡

ምርቶቹ በተገቢው ሁኔታ እንዲሰራጩ ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ ከማዕከል እስከ ወረዳ አስፈላጊው ድጋፍና ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

የምርት አቅርቦቱን፣ የግብይት ዋጋውን እንዲሁም የመሸጫ ቦታዎችን የማስፋት ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝም አስገንዝበዋል፡፡

በእንቁላል ላይ የሚታየውን የዋጋ ጭማሪ ግብረ-ሃይሉ ክፍተቱን ፈጥኖ በመገምገም ችግሩን እንዲፈታ አሳስበዋል፡፡

የበዓሉ ገበያ የተረጋጋና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ እንዲሳለጥም ሁሉም በባለቤትነት የድርሻው እንዲወጣ መጠየቃቸውንም የከተማዋ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.