Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በኮፊ አናን የመንገድ ደህንነት ሽልማት መድረክ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በኢስዋቲኒ እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የኮፊ አናን የመንገድ ደህንነት ሽልማት መድረክ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

በሽልማት መድረኩ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴዔታ በርኦ ሀሰን እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ሚኒስትር ዴዔታው÷ኢትዮጵያ የመንገድ ደህንነትን ለማስፈን ያደረገቻቸውን ጥረቶችን በመድረኩ እንደሚያቀርቡ ተጠቁሟል፡፡

በመድረኩ ለኢትዮጵያ እውቅና እንደሚሰጣት መገለጹንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኮፊ አናን የመንገድ ደህንነት ሽልማት በአፍሪካ ጎዳናዎች ላይ ሕይወትን ለማዳን የላቀ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ሀገራትና ባለድርሻ አካላትን እውቅና ለመስጠት የሚዘጋጅ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.