Fana: At a Speed of Life!

በ12ኛ ክፍል ፈተና ምንም ተማሪ ያላሳለፉ 700 ት/ቤቶችን ለማብቃት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምንም ተማሪ ያላሳለፉ 700 ትምህርት ቤቶችን ለማብቃት እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አድርገዋል።

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት እንደገለጹት÷ የመንግስት ትምህርት ቤቶችን በማብቃት ጥራት ያለው ትምህርት ለዜጎች ሁሉ ለማዳረስ እየተሰራ ነው።

በሁሉም መስክ ያለውን ችግር መፍታት የሚቻለው መሃንዲሶች፣ ቴክኖሎጂስቶች፣ ቴክኒሻኖችና ሌሎችን ባለሙያዎች በጥራትና በብቃት ማፍራት ሲቻል ነው ብለዋል፡፡

የት/ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል፣ መምህራንን አቅም በማሳደግና በሌሎች የአጠቃላይና ከፍተኛ ትምህርት ዘርፎች የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡

በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምንም ተማሪ ያላሳለፉ 700 ት/ቤቶችን ለማብቃት እቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው ማለታቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በበኩላቸው÷ በትምህርት ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት እጅግ ትልቁ ተግባር መሆኑን ጠቁመው፤ ከዚህ አንጻር እየተሰራ ያለው ስራ ተስፋ ሰጭ መሆኑን ተናግረዋል።

ትምህርት ላይ እየተደረገ ያለው ሪፎርም ሌሎችንም ተቋማት ሊቀይር የሚችል መሆኑን ነው የገለጹት የገለጹት፡፡

በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ችግር ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.