Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከአዲሱ የአፍሪካ ሕብረት አመራር ጋር በቅርበት እንደምትሠራ አረጋገጠች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካን የጋራ ተጠቃሚነት ለማሳደግ አዲስ ከተመረጡት የአፍሪካ ሕብረት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በቅርበት ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቀች፡፡

የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት 24ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው፡፡

በሕብረቱ የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ የአፍሪካን የጋራ ተጠቃሚነት ለማሳደግ አዲስ ከተመረጡት የአፍሪካ ሕብረት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በቅርበት ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡

አህጉሪቱ በአሁኑ ወቅት የአየር ንብረት ለውጥና ግጭትን የመሳሰሉ በርካታ ችግሮች እየተጋፈጠች መሆኗን ገልጸው፤ እነዚህን ፈተናዎች ለማለፍ ጠንካራ አመራር ያስፈልጋል ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

ምክር ቤቱ በስብስባው የአንድ የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ደኅንነት ምክር ቤት አባል ምርጫ እንደሚያካሂድ ተገልጿል፡፡

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የዓለም አቀፍ ሕግ አማካሪ አደረጃጀትና የአፍሪካ የህዋ ምክር ቤት በተመሳሳይ አንድ አንድ አባላት ያስመርጣሉ።

ምክር ቤቱ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የኢኮኖሚ ልማት፣ ቱሪዝም፣ ንግድ፣ ኢንዱስትሪ እና ማዕድን ኮሚሽን እና የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኮሚሽነር የምርጫ ሂደት አስመልክቶ የተዘጋጀ ረቂቅ ሪፖርትን ያዳምጣል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.