ከ10 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዟል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለ2017/18 የምርት ዘመን ግብዓት የሚሆን ከ10 ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ለምርት ዘመኑ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ወይም 24 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ገዝቶ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
በዚህም መሰረት እስከ ሚያዚያ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ከ10 ሚሊየን 343 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙ ተገልጿል፡፡
ከዚህም ውስጥ ከ8 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል በላይ የሚሆነው በድንበር ተሻጋሪ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ሲሆን ቀሪው ደግሞ በባቡር መጓጓዙን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል፡፡