አዲስ አበባ በዓለም የከተሞች ቱሪዝም ፌደሬሽን ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባ ከተማ አባል በሆነችበት የዓለም የከተሞች ቱሪዝም ፌደሬሽን የ2025 ዓመታዊ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው።
ጉባዔው እየተካሄደ የሚገነው በቻይና ሆንግ ኮንግ ከተማ ነው፡፡
በዚሁ ጉባዔ ላይም የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የአዲስ አበባ ከተማ የባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ኂሩት ካሳው (ዶ/ር) እና ሌሎችም የከተማ አሥተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።
ሐረር ከተማ በፈረንጆቹ 2023 የዓለም የቅርስ ከተሞች አባል ሆና መመዝገቧን ተከትሎ፤ ዘንድሮ በተካሄደው ጉባዔ የዓለም ቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን አባል ሆናለች መባሉን የአዲስ አበባ ከተማ የባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡