Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከቬይትናም ኮሙኒስት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቬይትናም ኮሙኒስት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ ጋር በፓርቲው ማዕከላዊ ጽሕፈት ቤት ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም፤ በተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ጉዳዮች ብሎም በሀገራዊ ልማት እና አሥተዳደር ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ እንዳመለከተው፤ ውይይቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እና ልዑካቸው በቬይትናም እያደረጉት ያለው ይፋዊ ጉብኝት አካል ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.