Fana: At a Speed of Life!

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ጋር ተወያይተዋል።

በሩዋንዳ የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ÷ ከፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ጋር በሁለቱ ሀገራት መከላከያ መኖር ስላለበት ግንኙነትና ትብብር በተመለከተ ውይይት አድርገዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋንጋ በክብር ዘብ የታጀበ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን÷ በሁለቱ ሀገራት መከላከያ ዙሪያ የሁለትዮሽ አካሂደዋል።

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ ጄኔራል ሙባረክ ሙጋንጋ በኢትዮጵያ ባደረጉት የስራ ጉብኝት ወቅት በሁለቱ ሀገራት መከላከያ መካከል በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ቀጣይ ትግበራ እና አፈፃፀም አቅጣጫ የሚያመለክት የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል።

ጉብኝቱ የረጅም ጊዜ የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር ትልቅ አንድምታ እንዳለውም ተገልጿል።

በተጨማሪም ሁለቱ ሀገራት በመከላከያ እና ሌሎች ተያያዥ ዘርፎች ላይ በአዳዲስ የትብብር መስኮች ለመሥራት እንዲሁም የቀጣናውን ሰላምና ደህንነት ለማሳደግ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያመላክት ነው ተብሏል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በጉብኝታቸው ወቅት ከሩዋንዳው መከላከያ ሚኒስትር ጁቬናል ማሪዛሙንዳ ጋር መነጋገራቸውን የመከላከያ ሰራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.