አሥተዳደሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ 200 ሺህ ወገኖች ማዕድ አጋራ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ 200 ሺህ ወገኖች ማዕድ አጋራ፡፡
ይህ ማዕድ ማጋራት በ2017 ዓ.ም ለ8ኛ ጊዜ የተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡
ማዕድ ማጋራት እርስበርስ መተሳሰብን የምናዳብርበት የሰው ተኮር እሳቤያችን ተግባራዊ ማሳያ ነው ያሉት ከንቲባዋ፤ ድጋፍ ላደረጉ የከተማዋ ባለሃብቶች፣ ተቋማትና ወጣት በጎ ፈቃደኞችንም አመሥግነዋል፡፡
በፍቅርተ ከበደ