የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ለ1 ሺህ 216 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መጪውን የትንሣኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 183 ወንዶች እና 33 ሴቶች ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ፡፡
ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች በክልሉ ባሉ ማረሚያ ቤቶች በሕግ ፍርድ አግኝተው ሲታረሙና ሲታነጹ ከቆዩ ታራሚዎች መካከል መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡
በዚሁ መሠረት የይቅርታ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ያሟሉ ስለመሆናቸው የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡