Fana: At a Speed of Life!

ከወርቅ ማዕድን ከ2 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት 9 ወራት ከወርቅ ማዕድን ከ2 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ መገኘቱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና እና ሠራተኞች ባለፉት 9 ወራት በተመዘገቡ ሀገራዊ አፈጻጸሞች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ባለፉት 9 ወራት ውስጥ 26 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መቅረቡ የተገለጸ ሲሆን፤ ከዚህም ከ2 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት መቻሉ ተመላክቷል፡፡

በማዕድን ዘርፍ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደ ምርት እየገቡ እንደሆነም ተመላክቷል።

ለአብነትም የሲሚንቶ ፋብሪካዎች፣ የወርቅ እና የድንጋይ ከሰል ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደ ምርት መግባታቸው ተነግሯል።

በውይይቱ የተገኙት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወጣቶችና ስፖርት አማካሪ ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ÷ የማዕድን ዘርፍ የላቀ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን ገልጸው፤ አመራሩ እና ሰራተኞች በስኬቱ ሳይዘናጉ ውጤቱን ማስቀጠልና ማላቅ ይገባቸዋል ማለታቸውን የማዕድን ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.