ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከቬይትናም ፕሬዚዳንትና ከብሔራዊ ም/ ቤቱ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቬይትናም ፕሬዚዳንት ጄነራል ሉዎንግ ኩዎንግ እና ከብሔራዊ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ትራን ታንህ ማን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቬይትናም ሶሻሊስት ሪፐብሊክ የሚያደርጉት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቀጥሏል፡፡
በዛሬው ዕለትም ከቬይትናም ፕሬዚዳንት ጄነራል ሉዎንግ ኩዎንግ እና ከብሔራዊ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ትራን ታንህ ማን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ስለ ሀገረ መንግሥት ቀጣይነት፣ የፖለቲካ ትብብር፣ የለውጥ ጥረቶች እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
በብዙ ዘርፎች የሁለትዮሽ ትስስሮችን እና ትብብሮችን ይበልጥ ለማጠናከር የሚቻልባቸው መንገዶች ተነስተው ውይይት እንደተደረገም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡