Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በሦስት ዘርፎች የተካሄዱትን የአፍሪካ ብየዳ ባለሙያዎች ውድድሮች አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በ3ኛው የአፍሪካ ብየዳ ፌዴሬሽን ዓመታዊ ጉባዔና ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ በተዘጋጀው የብየዳ ባለሙያዎች ውድድር በሦስት ዘርፎች አሸናፊ ሆነች፡፡
በሥራና ክኅሎት ሚኒስቴርና በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ላለፉት ሦስት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው ጉባዔ ዛሬ ተጠናቅቋል፡፡
በመድረኩ ላይ በአፍሪካ በብየዳ ዘርፍ ያሉ መልካም እድሎችና ተግዳሮቶችን በተመለከተ ውይይት መደረጉንና የዘርፉን ባለሙያዎች በማቀራረብ የልምድ ልውውጥ መካሄዱን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
ከጉባዔው ግን ለጎንም አፍሪካ በዘርፉ ያላትን ተወዳዳሪነትና ተቀባይነት ለማሳደግ ያለመ የብየዳ ባለሙያዎች ውድድር በሦስት ዘርፎች የተካሄደ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ በሦስቱም ዘርፎች አንደኛ በመሆን አጠናቅቃለች ብለዋል።
ደቡብ አፍሪካ ቀጣዩን ጉባዔ እንድታስተናግድ ተመርጣለች።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.