Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የሥርዓተ-ምግብ ፍኖተ-ካርታ አዘጋጅታ እየተገበረች እንደምትገኝ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) “ዘላቂ እና ህዝብን ማዕከል ያደረገ አረንጓዴ ሽግግር” በሚል ጭብጥ እየተካሄደ ባለው 2025 ፒ4ጂ ቬይትናም ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ልምዷን አካፍላለች።

በጉባኤው ከአረንጓዴ አብዮት ጋር የተጣጣመ ዘላቂ የሥርዓተ-ምግብ ሽግግር ላይ ያተኮረ የሚኒስትሮች መድረክ ላይ ኢትዮጵያ ልምዷን ማካፈል ችላለች፡፡

በጉባዔው ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የሥርዓተ-ምግብ ፍኖተ-ካርታ አዘጋጅታ እየተገበረች እንደምትገኝ ተገልጿል።

በተለይም ሀገር በቀል የአረንጓዴ አሻራ፣ የስንዴ ልማት እና የሌማት ትሩፋት ፕሮግራሞች ዘላቂ የምግብ ሥርዓትና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ግብርናን ለማረጋገጥ መሰረት እየጣሉ መሆናቸው ተመላክቷል።

ከመድረኩ ጎን ለጎን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከቬይትናም አቻቸው ጋር በግብርና ዘርፍ በተለይም በሩዝ ልማት ላይ በትብብር ለመስራት በመወያየት÷ የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.