Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 9 ወራት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ያስከበሩ ስኬታማ ሥራዎች ተከናውነዋል – አምባሳደር ነብያት ጌታቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ያስከበሩ ስኬታማ ስራዎች መከናወናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው አስታወቀ።

አምባሳደር ነብያት በሰጡት መግለጫ÷ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በፖለቲካና ኢኮኖሚ ዘርፎች እንዲሁም ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ መስኮች የተለያዩ ውጤታማ ሥራዎች መሠራታቸውን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላት ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያስችል ስራዎች መሠራታቸውን ጠቁመው÷ ከተለያዩ የአፍሪካና ሌሎች ሀገራት ጋር የጋራ ኮሚሽን ስብሰባዎች መካሄዳቸውን አንስተዋል።

በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ የውጭ ሀብት ፍሰትን ለማሻሻል የሚረዱ 143 መድረኮችን በማዘጋጀት ከ530 በላይ ኩባንያዎች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው የኢንቨስትመንት አድሎችን እንዲመለከቱ ተደርጓልም ነው ያሉት።

በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲያዊ ስራዎች በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎች እንዲመለሱ ከማድረግ ባሻገር የዜጎች መብትና ክብር እንዲጠበቅ መደረጉንም አምባሳደር ነብያት ተናግረዋል።

በአንዱዓለም ተስፋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.