Fana: At a Speed of Life!

ጸሎተ ሐሙስ ሥነ ሥርዓት በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጸሎተ ሐሙስ ሥነ ሥርዓት በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እየተከናወነ ነው።

በአዲስ አበባ ሀገረስብከት ልደታ ማርያም ካቴድራል ቤተክርስቲያን የሥነ ሥርዓቱ አካል የሆነው መስዋዕተ ቅዳሴ እየተካሄደ ይገኛል።

በቤተክርስቲያኒቱ ጸሎተ ሐሙስ በተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች የሚታሰብ ሲሆን÷ ሚስጥረ ቁርባን እና ሚስጥረ ክህነትም በፀሎተ ሐሙስ የተመሰረቱ ሚስጥራት መሆናቸው ይገለጻል።

የጌታ ራት፣ እፅበተ እግር እና የኢየሱስ ክርስቶስ የጌተሰማኒ ጸሎት ከፀሎተ ሐሙስ መርሐ ግብር ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው።

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.