Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ 5ኛውን የፒ4ጂ ጉባኤ ለማዘጋጀት ችቦውን በመረከቧ ኩራት ይሰማታል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በ2027 የሚካሄደውን አምስተኛውን የፒ4ጂ ጉባኤ ለማዘጋጀት ችቦውን በመረከቧ ኩራት ይሰማታል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ የሀኖይ ጉባኤ አነስተኛ ቢሆኑም በሚገባ የተቀናጁ የፒ4ጂ ፕሮጀክቶች ትርጉም ያለው ውጤት እንደሚያስገኙ እና ለማሳደግም ትልቅ አቅም ያላቸው መሆናቸውን አሳይቷል ብለዋል።

ይህን እድል በፅናት እና በቁርጠኝነት በመያዝ የቬይትናም፣ ኮሎምቢያ፣ ዴንማርክ እና የኮሪያ ሪፐብሊክ የታየውን ስኬታማ የዝግጅት ውርስ ጨምረን እናስቀጥላለንም ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ 2027 ጉባኤ ትብብር፣ ፈጠራ፣ አካታችነት እና ተግባር በተባሉት የፒ4ጂ አስኳል መርሆዎች በመመራት እንደሚዘጋጅም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

እንዲሁም ጉባኤው በአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ግብርና ብሎም ወጣቶችን እና ሴቶችን ማብቃትን የአረንጓዴ ሽግግር ወሳኝ አስፈፃሚ የማድረግ አስፈላጊነትን ትኩረት ሰጥቶ እንደሚዘጋጅ አመላክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.